ለአፍሪካ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆኑት ጥቃቅን እና መካከለኛ ኩባንያዎች በመሰል ተግዳሮቶች መፈተናቸው ከስራ እንዲወጡ ሊያስገድዳቸው እንደሚችልም ስጋትን ፈጥሯል፡፡ ቢዝነስ ኢንሳይደር በ2025 መጀመሪያ በአፍሪካ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያስመዘገቡ ሀገራትን ዝርዝር ባወጣበት መረጃው ኢትዮጵያን ቀዳሚ አድርጓታል፡፡ ...